ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት ሰበታ ስደርሱ የኢንስቲትዩቱ ማህበረሰብ፣ከፍተኛ የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና የተቋሙ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል፡፡ሚኒስትሩ ጉብኚታቸውን የጀመሩት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የአረንጓዴ አሻራ በተቋሙ ውስጥ የተተከሉ ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን፣በሴቶች ፎረም እየተሠሩ ያሉ የጓሮ አትክልቶችን፣ለወተት ከብቶች ኒዮስፖራ (Neospora caninum) በሽታ ላይ ለሚከናወን ጥናት ምርመር የሚውሉ ላሞችን በዶ/ር ማቴዎስ ላቀው ማብራሪያ የተሰጠበትን፣ዋና ዋና የንብ በሽታዎችን (Bee pest, varroosis, Nosemosis) ለመከላከል በሚረዱ ዘዴዎች ውጤታማነት ጥናት አፈፃፀም አሁናዊ ሁኔታ በአቶ ተስፋዬ ሙላት ማብራሪያ የተሰጠበትን፣ባዮሴፍቲ ደረጃ III ዞኖቲክ በሽታዎች ምርመራ ላብራቶሪ ፣የውሻ እብደት በሽታ ላብራቶሪ ፣ለበሽታ መከላከልና ቁጥጥር የሚረዳ መረጃ ማመንጨት/ማደራጀት/ናሙና ምርመራና መለያ/ላብራቶሪ፣ሞሌኩላር ላብራቶሪ በአቶ መላኩ ሶምቦ ገለጻ የተሰጠበት ፣የቫይሮሎጂና ባክቴሪሎጂ ሥራ ላብራቶሪ በዶ/ር ደመቀ ዘውዴና በአቶ አበበ ኦላኒ ገለጻ የተሰጠበት እና ዘረመል ላብራቶሪ ዙሪያ በዶ/ር ጌታቸው አቢቹ ገለጻና ማብራሪያ የተሰጠበትን ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡
ከመስክ ምልከታ ቀጥሎ የውይይት መድረክ ተደርጎ የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ተስፋዬ ሩፋኤል (ዶ/ር) የእንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኃላ አጠቃላይ የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት የሥራ እንቅስቃሴ አንኳር አንኳር ነጥቦችን፣ከተቋሙ የስራ ባህሪይ አንጻር ባልተመቻቼ መሠረተ ልማት በለሉ አከባቢዎች ስለሚሠሩ ረጅም ዓመታት አገልግሎት የሰጡ መኪኖች በመኖራቸው የሎጂስቲክ ችግሮች መኖራቸውን፣ለኬሚካል ግዥ በውጭ ምንዛሪ ስለሚገዙና ውድ በመሆናቸው በበጀት ዓመቱ የተመደበ በጀት በቂ አለመሆኑ እና ሁለት ተቋማት በመዋሀዳቸው ምክንያት ቢሮዎቹ ለስራ ምቹ አለመሆኑን በዝርዝር አንስተዋል፡፡
የእንስሳት ጠና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ጌትነት አቢ (ዶ/ር) የተቋሙን የኃላ ታሪክ ማዕከላዊ እንስሳት ጤና ላብራቶሪ ከ1987 -1989 ግ/ሚ/ር፣ብሔራዊ እንስሳት ጤና ምርምር ማዕከል ከ1989 – 1999 ኢግምድ አዋጅ ቁጥር 79/1989፣ብሔራዊ እንስሳት ጤና ምርመራና ምርምር ላብራቶሪ ከ2000 – 2013 ፣ብሔራዊ የቆላ ዝንብና ገንዲ በሽታ መቆጣጠሪያና ማጥፊያ ኢንስቲትዩት ከሐምሌ 2006 – ሚያዝያ 2014 ደንብ ቁጥር 304/2006፣እንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት አዋጅ ቁጥር 1263/2014 እና ደንብ ቁጥር 503/2014 እስካሁን ድረስ ተቋሙ የመጣባቸው መስመሮች መሆኑን ገለጻ አድረጓል፡፡
ጌትነት አቢ (ዶ/ር) አክለው ከተቋሙ ተግባራት መካከል ዋና ዋና የትኩረት ነጥቦች ብለው ያነሱት የእንስሳት ጤና ምርምር በተመለከተ ፡- ችግር ፈቺ ምርምር፣የቆላ ዝንብና ገንዲ በሽታ ቁጥጥር፣የእንስሳት ጤና ምርመራ አገልግሎት እና የምርመራና ምርምር አቅምን ማሳደግ ሲሆን ቅንጅታዊ አሠራርን በተመለከተ መንግስታዊ የልማት ተቋማት፣መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት ተቋማት፣ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ተቋማት፣ከፍተኛ የትምህርትና ምርምር ተቋማት ጋር ይሠራል ብሏል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ የውይይቱ ተሳታፊዎች አስተያየትና ጥያቄ ከተቀበሉ በኃላ ተዘዋውሮ ከተመለከቱት፣ ከተደረገላቸው ገለጻና ማብራሪያ መሠረት በማድረግ በማጠቃለያቸው ተቋሙ ትልቅ አቅም ያለው በመሆኑ ፕሮአክቲቭ (Proactive) ማድረግ ያስፈልጋልና እንደሀገር ብዙ ይጠበቃል፣ስራዎችን ማሳየትና ማጉላት ከእኛ ይጠበቃል፣ለእንስሳት ዘርፍ ትኩረት አልተሰጠም ማለት አንችልም ተቋሙ ስራዎቹን ከሌማት ትሩፋት ጋር ማያያዝ እንዳለባቸው፣በእንስሳት ዘርፍ ለሀገሪቱ አንኳር ተቋም ነው ስለዚህ ኦንላይን (Online) ማድረግ መቻል እንዳለበት፣ያለውን ትልቅ አቅም የማስተዋወቅ ስራ መሥራት፣በጀት ከመንግስት መጠበቅ ብቻ ሳይሆን የውስጥ ገቢን የማንጨት ስራ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት፣ከሌሎች ተቋማት ጋር አብሮ የመሥራት ጥቅሙ እኛ ጋ ምን አለ፣ምን የለም ብሎ ማሰብን የሚጠይቅ በመሆኑ ከግብርና ምርምር ባለስልጣን ጋር ተቀራርባችሁ ብትሠሩ ይህ ተቋም የሌለውን ግብርና ባለስልጣን ይኖረዋል ግብርና ምርምር ባለስልጣን የሌለውን እንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት ይኖረዋልና ቅንጅት ፈጥሮ መሥራት እንዳለብት አቅጣጫ በመስጠት ተጠናቋል፡፡