የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌትነት አቤ አቀባበልና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኃላ የቋሚ ኮሚቴውን ቼክ ሊስት መሠረት በማድረግ የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም፣ በአዲሱ ሪፎርም ተቋሙ ያለበትን ደረጃ፣ከቋሚ ኮሚቴው ከዚህ ቀደም የተሰጠው ግብረ መልስ በማስመልከት የተወሰደ እርምት፣ተቋሙን የገጠመው ተግዳሮቶች (በበጀት እጥረት እና የተመደበው በጀት ከተቋሙ ስራ ባህሪይ አኳያ በጊዜ አለመለቀቅ፣ የላብራቶሪ የመስክ ግብአቶች ዋጋ ንረት በግዥ በወቅቱ አለመቅረብ፣ የመስክ መኪኖች ረጅም ጊዜ አገልግሎት የሰጡ በመሆኑ ለባለሙያዎች ህይወት ስጋት መሆኑ)፣ የአርባ ምንጭ እና አሶሳ እንስሳት ጤና ምርምር ማዕከል የቢሮ ግንባታን በተመለከተ በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የመስክ ምልከታን በተመለከተ በተቋሙ ግቢ ውስጥ የሚገኘው ከርሰምድር ውሃ አገልግሎት አሰጣጥ፣ለምርምር የተዘጋጁ የንብ ቀፎ እንቅስቃሴ፣አረንጓዴ አሻራ ችግኞች ሁኔታ፣በሴቶች ፎረም እየተሠሩ ያሉት የጓሮ አትክልት እና የህፃናት ማቆያን ተዘዋውሮ ተመልክተዋል ልዑኩ፡፡
ከመስክ ምልከታ በኃላ የማጠቃለያ ውይይት ላይ በም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌትነት አቤ በቀረበላቸው ሪፖርት እና በመስክ ምልከታው መደሰታቸውን በመግለጽ ከግቢ ስፋት አንጻር የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቢኖረው እና መሬቱን ሙሉ በሙሉ መጠቀም ቢቻል፣ ከላብራቶሪ የሚወጡ ቆሻሻዎች ወደ ማህበረሰቡ እንዳይደርሱ ጥንቃቄ ቢወሰድ፣ አዲሱ ሪፎርም የተሻለ ስራ መሠራቱ መልካም ቢሆንም ወደ ተጨባጭ ስራ መገባት እንዳለበት እና በምርምር የተገኙ ውጤቶች ማህበረሰቡ ጋር እንዲደርስ ማድረግ እንዳለበት ዋና ዋና አስተያየት የተሰጡ ነጥቦች ናቸው፡፡