በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች የተሳፉበት እንደሀገር የተዘረጋውን የውይይት መድረክ ‘ከተረጂነት አስተሳሰብ መላቀቅ እና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ” በሚል ርዕስ የኢንስቲትየቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ተስፋዬ ሩፋኤል እና የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬከተር ዶ/ር ጌትነት አቢ በተገኙበት ውይይት እና ምክክር ተካሄደ፡፡
የመወያያ ጽሑፉን ያቀረቡት የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ገመቹ ጅጆ ሲሆኑ የገለፃው 1. ይዘት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ፖሊሲ መነሻዎች እና ማስፈንጠሪያዎች፣2. ከተረጂነት አስተሳሰብ መላቀቅ እና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚሉ ናቸው፡፡የውይይቱ ዋነኛ ዓላማ በሀገራችን ስር ሰዶ የቆየውን የተረጂነትና ልመና አስተሳሰብ በማስወገድ ህዝቡን ወደ ላቀ የምርታማነት ደረጃ ማሸጋገርና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ሀገር በቀል የአደጋ ስጋት አይበገሬነትን ለማረጋገጥ የፌዴራል ተቋማት ሚና መለየት እና መግባባት ነው ብሏል አቶ ገመቹ፡፡በመቀጠልም ተረጂነት ኢትዮጵያን የማይመጥን ክብረ– ነክ ልምምድ በመሆኑ ‘ተረጂነትን ማስወገድ ክብራችንና ነፃነታችንን እናስጠብቅ” የሚለው የቀረበው መወያያ ጽሑፍ Moto መሆኑን አስረድቷል፡፡
በመጨረሻም ከሠራተኞች በርካታ ገንቢ አስተያየቶች የተሰጠ ሲሆን ተረጂነት ገደብ ኖሮት በሀገራችን ልያበቃ እንደሚገባ እና በእልህና በወኔ ተነሳስተን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከተረጂነት መላቀቅ እንዳለብን ካስፈለገ ሁሉም ሠራተኛ በተመደበበት ስራ መስክ በትጋት በመሥራት ምርትና ምርታማነትን በእንስሳት ጤናው ዘርፍ ማሳደግ ይገባል የሚለው የዋና ዳይሬክተሩ እና የም/ዋና ዳይሬክተር የማጠቃለያ ሀሳብ ነው፡፡